ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና እነ አንዱዓለም አራጌ የይግባኝ ክርክራቸውን አጠናቀቁ

በታምሩ ጽጌ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በ18፣ በ25 ዓመታትና በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጥተው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) እና አንዱዓለም አራጌ ቅጣታቸውን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ላይ ከዓቃቤ ሕግ ጋር ታህሳስ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ክርክር አድርገው አጠናቀቁ፡፡