የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ውጤት አልባ መሆን የውጭ ኩባንያዎችን እየሳበ ነው

–    የፈረንሳዩ ቦሎሬ አፍሪካ ሎጂስቲክስ ለመንግሥት ጥያቄ አቀረበ

በዮሐንስ አንበርብር

ሦስት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማትን በማዋሀድ ግዙፉ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅቶ ሥራ ቢጀምርም፣ ውጤታማ ባለመሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ማኔጅመንቱን ለመረከብ አሰፍስፈዋል፡፡