በአዳማ የተጀመረው የምርጫ ዋዜማ ውዝግብ መቋጫ አላገኘም
– ‹‹ምርጫ ቦርድ ከኢሕአዴግም በላይ ኢሕአዴግ ሆኗል›› ቅሬታ አቅራቢ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች
በየማነ ናግሽየኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወያየት ከአንድ ወር በፊት ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አድርጎ በአዳማ ከተማ በተካሄደው ውይይት የተቀሰቀሰው ውዝግብ ቀጥሏል፡፡