መኳንንት እጆቻችሁን ከቤተ ክርስቲያን አንሡ
“አንስኡ እደዊክሙ መኳንንት እም ቤተ ክርስቲያን”
(መኑ ከማከ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ READ IN PDF)፦ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአዳም ልጆችን ለሰማያዊ ርስት
የምታዘጋጅ መንፈሳዊ ተቋም ናት፡፡ ባለቤቱ በማዕከለ
ምድር ቀራንዮ የተሰቀለበት፣ እርሷም ለጌታዋ ሙሽራ ሆና የምትኖርበት ምክንያት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በእንጨት ፍሬ የወደቀውን የአዳምን ዘር ወደ ቀደመ ክብሩ እና ቦታው መመለስ፡፡ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት ማሸጋገር ነው፡፡ በአርባ እና በሰማንያ ቀን ከተቀበልነው የልጅነት ሥልጣን አንሥቶ እስከ መጨረሻው የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ /ፕትርክና/ ያለው ሥልጣንና ኃላፊነት ሁሉም አንድ ዲናር ለማግኘት የምንሰራባቸው ናቸው፡፡ አንድ ዲናር አንድ መንግሥት አንድ ክብር በማለት ይተረጎማል፡፡

ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅና ለመምራት የተሾሙ
ሊቃነ ጳጳሳት፣ ገዳማቱን ተጠግተው
በማኅበር የሚኖሩ መነኮሳት፣ በየዋሻው በየፍርክታው የወደቁ መናንያን፣ በተቀደሰ ጋብቻ ፀንተው የሚኖሩ ሕጋውያን፣ በየአድባራቱ ለአገልግሎት የሚራወጡ ዲያቆናት ቀሳውስት፣ የቅኔ ማኅሌቱ መዘምራን፣ የወንጌልን ቃል
ለማዳረስ የሚደክሙ መምህራን፣ እነዚህ ሁሉ
በአንድነት ስለ አንድ ነገር ይደክማሉ፡፡ እርሷም መንግሥተ ሰማያት ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስም ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲጽፍ “ዘዓይን ኢርእየ፣ ወእዝነ ኢሰማዕ፣ ውስተ ልበ ሰብእ ዘኢተሀለየ ዘአስተዳለወ እግዚአብሔር ለዕለ ያፈቅርዎ፤ ዓይን ያላየው ጆሮም ያልሰመው በሰው ልብ ያልታሰበ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያዘጋጃት” ይላል፡፡

አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ “ኦ አንትሙ ሕዝበ ክርስቲያን በከመ ተጋባእክሙ
በዛቲ ዕለት ከማሁ ያስተጋብእክሙ በደብረ ጽዮን ቅድስት ወበኢየሩሳሌም አግዓዚት እንተ በሰማያት። እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ዛሬ በዚህች ዕለት
እንደተሰበሰባችሁ እንደዚህ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮንና በሰማይ ባለች ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ።” /ቅዳሴ ማርያም ቁ.156/ በማለት ስለመንግሥተ ሰማያት ይመሰክራል። በዚህች ዕለት ያለው ቀድሶ ያቆረበባትን ነው። በዚህች ዕለት በቤተ ክርስቲያን እንደተሰበሰባችሁ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮን ይሰብስባችሁ ከተፈጥሮተ እደ ሰብእ
ነጻ በምትሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊትም ይሰብስባችሁ ሲለን ነው፡፡ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ንጉሠ ሰማይ ወምድር ኢየሱስ
ክርስቶስ በስሙ አምነው በሃይማኖት ፀንተው፣ በምግባረ ሰናይ አጊጠው ለሚያልፉ ቅዱሳን ክብርን
የሚያድልባት ሥፍራ ናት፡፡

በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚደክሙ አበው በምድር ላይ የሚገጥማቸውን ፈተና አልፈው ወደ እርሷ ይገባሉ፡፡ ኃላፊነቱን ለሰጣቸው ጌታ ብቻ ሲታዘዙ ይህችን ርስት ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡ ምእመናንም በሃይማኖት በምግባር ሲፀኑ “ንዑ ሀቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ፤ እናንት የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ
ኑ” የሚል ድምጽ ይሰማሉ፡፡ ሐዋርያት ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል እያሉ የመሰከሩት ለዚህ ነው፡፡ በዓላውያን ፊት የፀኑት እርሷን
/መንግሥተ ሰማትን/ በማሰብ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን ቅዱሳን ሐዋርያት ቀጥሎም አበው ሐዋርያት፣ ከዚያም ሊቃውንት፣ ሁሉም በየዘመናቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት በብዙ መከራ
ነበር፡፡ በእሳት ተቃጥለው፣በመጋዝ ተሰንጥቀው፣ ለአናብስት ተሰጥተው ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡ አደራቸውን
በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ልቡናቸውን በሰማያት አድርገው ስለሚጓዙ በዓላማ በአቋም የፀኑ ነበሩ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን ዋጋ እያሰቡ ሁሉንም በአኮቴት ይቀበሉም ነበር ፡፡

በዘመናችን
እንደ ቀደሙ ሐዋርያት ያለ ጽናት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያት ማሰብ፣ መሥራት ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡ አላውያን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይቀርቡ፣ለመንፈሳዊው አገልግሎ እንቅፋት እንዳይሆኑ መሪዎች ትጉኅ እረኛ መሆን ይገባቸዋል፡፡ሐዋርያው “እንዲሁ ሰው እኛን እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቁጠረን፡፡ እንደዚህም ሲሆን በመጋቢዎች ዘንድ ታማኝ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል፡፡” (1ቆሮ
4-1) እንዳለ መሪዎች ለተጠሩለት ዓላማ ታማኝ ሊሆኑ ግድ ይላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጠንካራ መሪ ሲጠፋ ቤተ ክርስቲያን የመናፍቃንና፣ የዓላውያን መረማመጃ፣ አጥር እንደሌለው ቤት የኃላፊ አግዳሚው መውጫ መውረጃ ትሆናለች፡፡ መንፈሳዊ ተቋም የሚለው በጽሑፍ የሚነበብ ብቻ ይሆንና በተግባር ግን ምድራዊውን
ፖለቲካ መፈፀሚያ ማስፈፀሚ ወደ መሆን ትሸጋገራለች፡፡

ሰሞኑን
በሁለቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት በብዙዎች ልቦና ተስፋን የጫረ ነበር፡፡ ውጤቱ እንዲሰምርም ሁሉም በየሥፍራው የተዋሕዶን አምላክ እየለመነ ነበር፡፡ ነገር ግን ችግሩን እግዚአብሔርና ጥቂት ግለሰቦች በሚያውቁት ምክንያት የታሰበው ሁሉ እንዳልታሰበ ሆኖ መምጣት ጀመረ፡፡ ታሪክ ሠርተው ቀንበራችንን ይሰብራሉ ያልናቸው አበው ሌላ የብረት ቀንበር ሊጭኑብን እየተዘጋጁ ለምርጫም እየተጣደፉ መሆናቸውን
ሰማን፡፡ በጉዳዩም እጅግ እጅግ አዘንን፡፡ ሌላ ሠላሳና አርባ የልዩነት ዓመት ለማምጣት ከመቻኮል አንድነቱን ማስቀደም የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጭ መሆን ነበረበት፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡

ለመሆኑ
በዚህ ጉዳይ ማንን እንጠይቅ? እነዚያ ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲራወጡ የምናውቃቸው
አባቶች በፍጥነት ሐሳባቸውን የቀየሩበት ምክንያት ምንድን ነው ብለን እንገምት? በብዙዎች እምነት ይህ ድርጊት ያልታወቀ እጅ ያለበት
ነው፡፡ከአባቶች ጀርባ ሌላ አካል አለ እየተባለ ነው፡፡ ይህ እጅ የመንግሥት እጅ እንደሆነም መነገር ከጀመረ ውሎ
አደረ፡፡ ጉዳዩ እውነት ከሆነ፣ እና የመንግሥት አካላት እጃችሁን አስገብታችሁ ከሆነ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን:: መኳንንት እጆቻችሁን አንሱልን እንላለን፡፡ እናንተ ከምትጋደሉለት ዓላማ በብዙ ሺህ እጥፍ የሚበልጥ ሰማያዊ ዓላማና ሥልጣን አባቶች እጅ አለ፡፡ እነዚህን አባቶች ከሰውም ከእግዚአብሔርም እንዳታጣሉ መኳንንት
እጆቻችሁን ከዚህች ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ አንሱ፡፡ የሃይማኖት ነጻነት እንዳለ በሚነገርበት አገር ይህንን ማድረጉ ተገቢ አይደለምና መኳንንት እጆቻችሁን አንሱ፡፡

በእናንተ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ የሃይማኖት
ሰዎችን አጥብቃችሁ እንደምትኮንኑ ሁሉ በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ ስትገቡ ቅሬታችን ወሰን የለውም፡፡ እነዚህን አባቶች የሾመ ሰማያዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ለአገልግሎት የተጠሩት፣ የመነኮሱት፣ ለጵጵስና ማዕረግ የበቁት እርሱን
ሊያገለግሉ እንጂ የእናንተ መሳሪያ ሊሆኑ አይደለም፡፡ እንደ ሰናኦር ሰዎች ተግዳሮታችሁ ከፈጣሪ ጋር እንዳይሆን
መኳንንት እጀቻችሁን አንሱ፡፡ የቄሣርነት ድርሻ ለእናንተ ይበቃል የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መልሱ፡፡ ይህ መልእክት እጃችሁ ካለበት ይድረሳችሁ፡፡ ከሌላችሁበት እንቀጥላለን፤ ፈጣሪን በጸሎት እየተማፀንን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም የልጅነት ጥያቄያችንን እናቀርባለን፡፡ ለመሆኑ ይህች እጅ የማን ናት?፡፡ ለአንድነቱስ እንቅፋት የሆነ ማን ነው? የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ጥያቄ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር