ባህር ዳር የፌደራል ከተማ እንደምትሆን መነገሩ ተስተባበለ

‹‹የባህር ዳር የመሬት ዋጋን ለማናር ሆን ተብሎ የሚወራ ነው›› የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ

በብርሃኑ ፈቃደ

የባህር ዳር ከተማ ወደ ፌደራል ከተማነት በመዛወር እንደአዲስ አበባና ድሬዳዋ የከተማ አስተዳደር እንደምትሆን ቢነገርም፣ የከተማው አስተዳደር ሐሰት መሆኑን በመግለጽ አስተባበለ፡፡