ኢትዮጵያ ዘረመሉ የተሻሻለ የጥጥ ዘር በሚቀጥለው ዓመት ለምርምር ማብቀል ልትጀምር ነው

በምዕራፍ ብርሃኔ

አገሪቷ ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱትሪ እንድታስገባ የታቀደላትን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማሳካትና በዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን፣ ዘረመሉ ተሻሽሎ ተሠርቶ ‹‹ቢቲ ኮተን›› በመባል የሚጠራውን የጥጥ ዘር  በሚቀጥለው የምርት ዘመን ለምርምር ማብቀል ልትጀምር እንደምትችል የጉዳዩ ባለቤት ከሆኑ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡