በአቶ ጁነዲን ባለቤትና በሽብርተኝነት በታሰሩ ተጠርጣሪዎች ክስ ላይ ብይን ተሰጠ

–    ከቀረቡት ስምንት የክስ መቃወሚያዎች ሁለቱ ተቀባይነት አገኙ

በታምሩ ጽጌ

ከጄነራል ዊንጌት ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አወሊያ ትምህርት ቤትና መርካቶ አንዋር መስጊድ፣ ሐምሌ 6 እና 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረው ረብሻና በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጽመዋል በተባሉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች፣ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ በቁጥጥር ሥር በዋሉ 29 ግለሰቦችና ሁለት ድርጅቶች ላይ ቀርቦ በነበረው የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ላይ ከትናንትና በስቲያ ብይን ተሰጠ፡፡