‹‹ተቀናቃኞቹ እስራኤልና ኢራን በኤርትራ ወታደራዊ ካምፖች መሥርተዋል›› ስትራትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ለረዥም ጊዜ የቆየና ሥር የሰደደ የፖለቲካ ፍጥጫ ውስጥ የሚገኙት እስራኤልና ኢራን የቀይ ባህር አካባቢን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ፉክክር ማየሉን፣ ለዚህ ፍላጐታቸውም በኤርትራ ወታደራዊ ካምፖችን ማቋቋማቸውን መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ወታደራዊ የስለላ ድርጅት ስትራትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ገለጸ፡፡