የ “24 ቀበሌ ልጆች” በይግባኝ ከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደተወሰነባቸው ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

–    ሁለቱ ፍርደኞች በሌሉበት ነው የተቀጡት

በታምሩ ጽጌ

በተከሰሱበት የተለያዩ ወንጀሎች ማስረጃ አልቀረበባቸውም በማለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት በነፃ ያሰናበታቸውና የተወሰነ ዓመታት በጽኑ እስራት ተቀጥተው የነበሩ በተለምዶ የ24 ቀበሌ ልጆች በመባል የሚታወቁት፣ በይግባኝ ከስድስት እስከ 18 ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ እንደተወሰነባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡