ነግ በኔ?… (ቁጥር አንድ)
ከግርማ እንድሪያስ
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከጠ/ሚ/ር ፍቅረስላሴ ወግደረስ ምን ይማራሉ?
… ጠ/ሚ/ሩ አጋሮቻቸውንና እኩዮቻቸውን በማሰባሰብ ወደ ከርቼሌ ወረዱ። እስረኞቹን ለመጎብኘት። የፖሊስ ሰራዊቱም፣ የመከላከያውም አዛዦች ተከተሏቸው። በወቅቱ፤ ከረጅም የስልጣን አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጎዜ በ ‘ትልቅ’ ባለስልጣን እንደተጎበኘ የተነገረለት ይህ ወህኒ ቤት ከወግደረስ ልጅ ስጦታም ቢጤ ተበርክቶለት ነበር። ዛሬም ድረስ የሚወራለት ስጦታ!…