የኃይማኖት ነጻነት ጥብቅና በኢትዮጵያ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ለውድቀት የተዳረገው የኃይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያ
በዚህ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ “አንድነት ለኃይማኖት” በሚል ጽሁፍ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው የኃይማኖት ነጻነት ገፈፋ ያለኝን ስጋት ገልጬ ነበር። በዚህም ሳቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲሱ የሰብአዊ መብት መጣስ አካሄድ በኃይማኖት ነጻነት ላይ ማነጣጠሩን አሳስቤያለሁ። ስጋቴን ትንሽ ቀለል ያረገልኝ ስርአት የተላበሱት የክርስቲያኑና የሙስሊሙ የኃይሞነት መሪዎች በኃይማኖት ውስጥ የሚሞከረውን አግባብነት የሌለውን ጣልቃ ገብነት ጠንክረው መቃወማቸውን በማየቴ ነበር።