የአዲስ አበባ አስተዳደር የሚድሮክ እህት ኩባንያን አስጠነቀቀ

–    23 የወረዳ አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል
–    163 አመራሮችም እየተመረመሩ ነው

በታምሩ ጽጌ

የሚድሮክ እህት ኩባንያ የሆነው ሁዳ ሪል ስቴት ከ15 ዓመታት በፊት መሀል ፒያሳ ላይ ወስዶ ያጠረውን መሬት ግንባታ የማይጀምርበትና በፍጥነት ገንብቶ የማያጠናቅቅ ከሆነ፣ አስተዳደሩ ተረክቦ ለልማት እንደሚያውለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አስታወቁ፡፡