የጀግና ዎሮታ በሰለሞን ለማ ገመቹ – አዲስ መጽሃፍ በገበያ ላይ

“የጀግና ወሮታ” የተሰኘው ፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት የጦር ሜዳ ህይወት የሚያስቃኘው መጽሀፍ ለንባብ በቅቷል።ይህ በፈጸመው የጦር ሜዳ ጀብዱ ‹የጀግና ሜዳሊያ› ተሸላሚ በሆነው በመቶ አለቃ በቀለ በላይ ህይወት ዙርያ የሚያጠነጥነው መጽሀፍ ከተለመደው መንገድ ወጣ ባለ መልኩ ‹ያልተዘመረላቸውን› ተራ ወታደሮችና ባለ አንስተኛ ማዕረግ አዛዦች የጦር ሜዳ ህይወት ያስፈትሻል።

የአገሪቷን ዳር ድንበር ለማስከበር ከበርሀ በርሀ ሲንከራተቱ የኖሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች የተሸከሙትን ቀንበር ልክ ፤ ተጋድሎና ጽናታቸውን ፣ በመጨረሻም የጠበቃቸውን መከራ የሚዘክረው “የጀግና ወሮታ” ሰሞኑን የቀድሞው ሰራዊት ከፍተኛ የጦር አዛዦች በተገኙበት በአገር ፍቅር አዳራሽ ተመርቋል።መጽሀፉን በውጪ አገራት ለማከፋፈል የምትፈልጉ ሁሉ ደራሲውን ጋዜጠኛ ሰለሞን ለማ ገመቹን በሚከተለው የኢሜይል አድራሻው ልታገኙት ትችላላችሁ። (የጀግና ዎሮታ በሰለሞን ለማ ገመቹ)