ተቃዋሚዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መነጋገር ይፈልጋሉ

ሰላሣ ሦስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዓመት የሚደረገው የአካባቢ ምርጫና ወደፊትም የሚካሄዱት ምርጫዎች እንደ 2002 ዓመተ ምኅረቱ ከሆኑ ለአገሪቱ ህልውናም አስጊ ናቸው አሉ።