ጅንአድ በዶዶላ ይዞታዬ ሥር የነበረ መሬት ተወስዶ ተሸጠብኝ አለ

–    ሰባት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘይት ለማከፋፈል እንዳልቻለም ገለጸ

በዳዊት ታዬ

መንግሥታዊው የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ) ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ አንዳንድ ቅርንጫፎቹ ለአደጋ የተጋለጡበት መሆኑን፣ በተለይ ደግሞ በዶዶላ ከተማ ከሚገኘው ይዞታው ላይ የከተማው አስተዳደር ቦታ ወስዶ ለግለሰብ እንደሸጠበት ገለጸ፡፡