ከንቲባ ኩማ የመንገድ ሥራ ተቋራጮችን አስጠነቀቁ

በታምሩ ጽጌ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እያስገነባቸው ካሉት ከ30 በላይ የሚሆኑ መንገዶች ውስጥ አሥሩን የጐበኙት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ፣ በገቡት ውል መሠረት ሥራቸውን ማጠናቀቅ ያልቻሉትን ኮንትራክተሮች አስጠነቀቁ፡፡