ሰመጉ በለገጣፎ ከ15 ሺሕ በላይ ይዞታዎች በሕገወጥ መንገድ ተሸጠዋል አለ

–    ወቀሳው የተሰነዘረባቸው ኃላፊዎች ተነስተዋል

በዮሐንስ አንበርብር

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ከአዲስ አበባ በ21 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የአስተዳደር ችግሮችና ሕገወጥ የመሬት ሽያጭ መስፋፋቱን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) አስታወቀ፡፡