የሕዝብ ራዕይ ለምን በአምባገነን ስም ይጠራል?
የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ
አቶ ኃይለማርያም ”የታላቁን መሪ ራዕይ“ እንደሚተገብሩ ቃል ገብተዋል፤ ለውጥ እንደሚያደርጉ ግን አልገለፁም። ኢህአዴግ በአቶ መለስ ፍላጎት ብቻ ይመራ፣ የኢትዮጵያ ህዝብም በሰውየው ፍላጎት ይገዛ ነበር። ከዛ ፍላጎት ማፈንገጥ ለግምገማ ያጋልጥና በጠላትነት ያስፈርጅ ነበር። ያገዛዙ ጠባይ በድርጅቱ አባላትም አለመተማመንን አስርፆና አስፍኖ፣ አባላቱ በግልፅ ሃሳባቸውን እንዳይገልፁ አፍኖ ስለቆየ ኢህአዴግ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላም እስካሁን የሚመራው በሟቹ መንፈስ ነው። አባላቱ ከአፋኙ ባህል ገና አልተላቀቁም። ስለዚህ የአቶ ኃይለማርያም ንግግር የተጀመረውን መቀጠል ከሚለው ሃሳብ አለመውጣቱ ለጊዜው አያስገርምም።