እኛም ሁላችንም “አበበ በቀለ” ነን!

አበበ በቀለ

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ሦስት ነገሮችን በጥልቀት ብዙ ሳሰላስል ነበር። በመጀመሪያ የከነከነኝ ነገር አንዲት አቢጌል የምትባል የአራት ዓመት ሕፃን ስለ “ብሮንኮ ባማ እና ሚት ራምኒ” በሬዲዮ መስማት እንደሰለቻት ለእናቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ስትናገር ማየቴ ነው። የዚህች ሕፃን ቪድዮ በዩቱብ ከ16 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አይቶታል።