ሦስቱ እህትማማች ኩባንያዎችና የዘር ማባዛት ኢንቨስትመንታቸው

በዳዊት ታዬ

ለተለያዩ ሰብሎች ግብዓት የሚሆኑ ምርጥ ዘር የሚያመርቱ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አድካሚውን የግብርና ዘርፍ እንደ ቋሚ ሥራ ይዞ ወደ ገጠር ለመግባት የሚደፍር ጥቂት ነው፡፡