ገቢዎች ባለሥልጣን የታክስ ተከታታዮችን ማሰማራቱን ቀጥሏል

በዮሐንስ አንበርብር

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታክስ ማጭበርብርና የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴን ለሚጠቁም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወሮታ ለመክፈል ከጀመረው እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ በባለሥልጣኑ አጠራር “ተባባሪ” እና “ያዥ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን የታክስ ክትትል ሠራተኞች በመመልመልና በማሠልጠን ማሰማራት ቀጥሏል፡፡