ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብዛት ላይ የወጣውን ዓለም አቀፍ መረጃ ነቀፉ
በታደሰ ገብረ ማርያም
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ. በጁን 2011 ባወጡት የጋራ ሪፖርት የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ቁጥር ከጠቅላላው ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር 17.6 በመቶ (14 ሚሊዮን) ይሆናል ብለው ያወጡት መረጃ፣ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ያልተጠናና በአካል ጉዳት ዓይነቶች ዝርዝር መረጃ ላይ የተጠናከረ አይደለም በማለት ክፉኛ ተቃወሙት፡፡