ኃላፊነቱን የማይወጣ ባለሥልጣን እንዲወገድ ፓርላማው ግፊት አደርጋለሁ አለ
– መንግሥት ተግባራዊ ዕርምጃ እንዲወስድ እየተጠየቀ ነው
በውድነህ ዘነበ
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሚመለከት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በቅርቡ በተካሄደው ስብሰባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ችግሮቹን እንዲያርም ተነግሮት ማስተካከል ያልቻለ ኃላፊ ከሥልጣኑ እንዲነሳ ፓርላማው ግፊት እንደሚያደርግ አስታወቁ፡፡