መንግሥት ምዕራባውያን ፍትሐዊ የገበያ ዕድል እንዲሰጡ ጠየቀ
• በኢትዮጵያ የመሬት ሽሚያ የለም አለ
በብርሃኑ ፈቃደ
ዋና መሥርያ ቤቱን በኔዘርላድስና በቤልጅየም ያደረገው ዓለም አቀፍ የእርሻና የገጠር ልማት ማዕከል ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ትናንት ከተከፈተ በኋላ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ ምዕራባውያን ለታዳጊ አገሮች ፍትሐዊ የገበያ ዕድል እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡