በቂም በቀል ተነሳሰቶ ጎረቤቱን የገደለው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም

• የሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል

• አንድ የክልል ባለሥልጣን ለገዳዩ ከለላ ሰጥቶታል ተብሏል

በሸዋዬ ካሳሁን

Ethiopia Zare (አርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008) ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ራያ ቆቦ በተባለው ከተማ በቂም በቀል በመነሳሳት የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ሊውል ባለመቻሉ በየሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል።