የመድረክ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱ ዘጠኝ ሰዎች ጥፋተኛ ተባሉ
“ባለቤቴ ከሥራ እንድትወጣ በመደረጓ ልጆቼ ያለገቢ ለመኖር ተገደዋል” የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ
በታምሩ ጽጌ
ከሁለት ዓመታት በፊት ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የመድረክ ሥራ አስፈጻሚና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ መምህር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡