መንግሥት የነዳጅ ማጣርያ ለመገንባት ከደቡብ ሱዳን ጋር አልተስማማሁም ሲል አስተባበለ

•    ኬንያ ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም ማለቷ ተሰማ

በብርሃኑ ፈቃደ

የሁለቱን ሱዳኖች ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ ጉብኝት ተከትሎ የዜና አውታሮች በተለይ ከደቡብ ሱዳን ጋር የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ማጣርያ ለመገንባት መስማማቱን በመጥቀስ ቢዘግቡም፣ ይህ ከእውነት የራቀ ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡