ለወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎና ትስስር የተጀመረው ጥረት

በየማነ ናግሽ

እስካሁን በዓለማችን ከተካሄዱ አብዮታዊ ለውጦች ከበስተጀርባ ወጣቶች አሉበት፡፡ ብዙዎች እንደሚስማሙበት ያለ ወጣት የሚታሰብ መሠረታዊ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ለውጥ እስከዚህም ነው፡፡