ኢትዮጵያውያን ያልተሳተፉበት የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

በቃለየሱስ በቀለ

ተቀማጭነቱ በስፔን የሆነው ሲንጉላ ሪስ አድቫይዘርስ የተባለ ኩባንያ ዋይኤችኤም ኮንሰልቲንግ ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ባለፈው ሳምንት የሦስት ቀናት የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ በሒልተን ሲያካሂድ፣ በስብሰባው ላይ አንድም የኢትዮጵያ ኩባንያ እንዳልተሳተፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡