ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሻሸመኔ የሚገኘውን በቀለ ሞላ ሆቴል ገዝቶ እየገነባ ነው

በዮሐንስ አንበርብር

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሐዋሳ ከተማ ላይ በከፍተኛ ወጪ ገንብቶ ሥራ ከጀመረው ሪዞርትና ሆቴል በተጨማሪ፣ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የሻሸመኔ በቀለ ሞላ ሆቴል በመግዛት፣ በአካባቢው የሪዞርትና ሆቴል ንግድ ሥራ ላይ ያለውን ድርሻ እያጠናከረ ነው፡፡