የኦሮሚያ ክልል በመሬት ሊዝ መነሻ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው

በውድነህ ዘነበ

የኦሮሚያ ክልል በከተማ መሬት ላይ የሊዝ ዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡ ክልሉ በፌዴራል ደረጃ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ መሠረት ተጨማሪ ከተሞችን በሊዝ ሊያካትት መሆኑ ታውቋል፡፡