መንግሥትን 18 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቷል የተባለ የዕርዳታ ድርጅት ኃላፊ እየተፈለገ ነው

በዮሐንስ አንበርብር

ፍትሕ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ በጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ ኢትዮጵያን 18 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አሳጥቷል ብሎ የጠረጠሩትን ዘ ግላድኒ ሴንተር ፎር አዶፕሽን የተባለ የአሜሪካ የማደጎ ድርጅት የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የነበረ ግለሰብን እያደኑ ነው፡፡