የልጆቹን እናት በበርካታ ጥይቶች ደብድቦ ለገደለው ተጠርጣሪ ተመጣጣኝ ቅጣት ተጠየቀ

‹‹ልጃችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመገደሏ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደን››  የሟች ቤተሰቦች

በታምሩ ጽጌ

ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ማለዳ ሁለት ሕፃናት ልጆቿን ወላጆቿ ቤት አድርሳ ወደ ሥራዋ በመሄድ ላይ የነበረችውን ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታደሰን በመኪና አሳዶ በክላሽንኮቭ ጠመንጃ በርካታ ጥይቶችን በመተኮስ፣ ገድሏታል በተባለው ተጠርጣሪና የቀድሞ ባለቤቷ አቶ የወንድወሰን ይልማ ላይ ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጣል ቤተሰቦቿ ጠየቁ፡፡