የልጆቹን እናት በጥይት ደብድቦ ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

–    የሟች እናትና ሁለት ግለሰቦች ቆስለው መትረፋቸው ታውቋል

በታምሩ ጽጌ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፣ ላፓሪዚያን ካፌ ፊት ለፊት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡15 ሰዓት ላይ የልጆቹን እናት በጥይት ደብድቦ ገድሏል የተባለው ግለሰብ፣ እዚያው በቁጥጥር ሥር መዋሉን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡