ኢሰመጉና የሴቶች ሕግ ባሙያዎች ማኅበር ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ተወረሱ
በታምሩ ጽጌ
የፌዴራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ እንዳያንቀሳቅሱ ያገደባቸውን ገንዘብ በሚመለከት፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው የነበሩት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ኢሴሕባማ) ይግባኛቸው ውድቅ ሆኖ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲወረሱ ጥቅምት 9 ቀን 2005 ዓ.ም. ተወሰነ፡፡