ከፈረሰው መርካቶ ሲቲ ባንክ አክሲዮን የገዙ ገንዘባችንን የሚመልስልን አጣን አሉ

በታምሩ ጽጌ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ ባንክ ስለማቋቋም ባወጣው መመርያ ምክንያት የፈረሰው የመርካቶ ሲቲ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች ገንዘባችንን የሚመልስልን አጣን አሉ፡፡ “ገንዘባችንን እናጣለን” የሚል ሥጋት እንዳደረባቸውም ለሪፖተር ገልጸዋል፡፡