የሻዕቢያ መንገድ

Berket Simon, በረከት ስምኦንተስፋዬ ገብረአብ

 የኤርትራውያን የአረብኛ ፓልቶክ ክፍል በረከት ስምኦንን እንግዳ አድርጎ ጋብዞ ነበር። ጥያቄዎች ይቀርቡ የነበሩት በአረብኛ ቢሆንም፣ የትግርኛ ትርጉም ስለነበረው ሙሉውን ተከታትዬው ነበር። ውይይቱ ሲጨመቅ በሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር ማለት ይቻላል።

የመጀመሪያው፣ “የኢትዮ – ኤርትራ ድንበር ለምን አይካለልም? ችግራችሁ ምንድነው?” የሚል ነበር። በረከት የተለመደውን ምላሽ ሰጥቶአል።