ለፕሬስ ነፃነት እንቆማለን! ሕዝባችንን እናገለግላለን! መስዋዕትነት ለመክፈል ቃል እንገባለን! እናመሰግናለን!

ጋዜጣችን ‹‹ሪፖርተር›› አሥራ ሰባተኛ ዓመትዋን እያከበረች ናት፡፡ አሳታሚ ድርጅታችን ሚድያ ኤንድ ኮሙዩኒኬሽንስ ሴንተር ከአሥራ ሰባት ዓመት በፊት በመስከረም መጀመሪያ የመጀመሪያዋን ቅፅ አንድ ቁጥር አንድ ሲያሳትምና ሲያሰራጭም ሆነ፣ አሁን ከአሥራ ሰባት ዓመታት በኋላ ይህን ቅፅና ቁጥር ሲያሳትምና ሲያሰራጭ በዓላማው፣ በተልዕኮውና በአሠራሩ አንድና አንድ ግልጽና ግልጽ ነው፡፡