ሼክ አል አሙዲና ሸሪኮቻቸው በጨረታ ላሸነፉዋቸው ድርጅቶች አሁንም ክፍያ አልፈጸሙም

–    የአዶላ ወርቅ ማምረቻና አሥር ድርጅቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ

በዳዊት ታዬ እና በውድነህ ዘነበ

ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ አራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለመግዛት የጨረታ አሸናፊነታቸው የተገለጸላቸው የሼክ መሐመድ አል አሙዲና ሸሪኮቻቸው ኩባንያዎች የቅድሚያ ክፍያ ጊዜ ቢራዘምላቸውም፣ በተፈቀደላቸው ቀነ ገደብ ያለመክፈላቸው ተገለጸ፡፡