እንኳን ደስ አለን! ይልመድብን!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰሞኑን እንደገና ምን ዓይነት ወርቅ ሕዝብ ነው የሚያሰኝ ሕዝባዊ ትርዒት አሳይቷል፣ አይቷል፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አለብን ሲል ሰነበተ፡፡ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለብሔራዊ ቡድናችን እናደርጋለን አለ፡፡ ለማድረግም ሲዘጋጅ ሰነበተ፡፡