ጁነዲን፣ ኦህዴድ እና ኢህአዴግ
(ልዩ ጥንቅር- በደረጀ ሀብተወልድ – ኢሳት)
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶና አራት ባለስልጣናት፤ ከኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚነት ሰሞኑን ተነስተዋል። ሚኒስትር ጁነዲንና አራቱ አመራሮች ከሥራ አስፈፃሚነታቸው እንዲነሱ የተወሰነው፤ የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ካለፈው መስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው።