የሥነ-ምግባር መሠረት – “ብፁዓን ንጹሓነ ልብ”

ብፁዓን ንጹሓነ ልብ - እጓለ ገብረዮሐንስ (ዶ/ር)ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

ያ ሰው ሞተ አሉኝ፣ እንዴት ያ ሰው ይሙት?

በሕይወት ሲያስተምር፣ ለሰው ልጆች ሕይወት፣

ተቀበረ አሉኝ፣ ከቶ እንዴት ይቀበር፣

ሙት ሕያው እንዲሆን፣ በቁሙ ሲያስተምር!

(“ስለ ክርስቲያን ሥነ-ምግባር መሠረት” (ብፁዓን ንጹሓነ ልብ)፤ ገጽ 165)

ከወራት በፊት “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” (ዘየአውዱት ከመ ዳመና)”ን ባወጣሁ ጊዜ እንደገለጽኩት፣ “የዶ/ር እጓለ ባለቤት ከባሕር ማዶ መጥተው፣ “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” የተባለውን መጽሐፍ በድጋሚ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት እያሳተሙት መሆኑንና በቅርቡ እንደሚወጣም ጓደኛቸው ዶ/ር ምክረሥላሴ አበሰሩኝ ስል ጽፌ ነበር። በተጨማሪም፣ ደራሲው የአባታቸውን፣ የአለቃ ገብረ ዮሐንስ ተሰማንም ታሪክና ስራዎች የሚዘክር መጽሐፍም አዘጋጅተው ስላለፉ፣ እርሱም ጭምር ከላይ በተጠቀሰው ማተሚያ ቤት እየታተመ እንዳለና መገባደጃውም ላይ እንደሆነ” ዶ/ር ምክረሥላሴን በመጥቀስ ጽፌ እንደነበረ የሚታወስ ነው።