ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት በሚጋሯቸው ገቢዎች ላይ ጥያቄ አነሱ

በዮሐንስ አንበርብር

ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚጋሯቸው የተለያዩ የገቢ ዓይነቶች መከፋፈያ ቀመር ጊዜው ያለፈበትና አሁን ያለውን የዕድገት ደረጃ ያላገናዘበ በመሆኑ እንዲሻሻል ጥያቄ አቀረቡ፡፡