አቡነ ገሪማ ከሥራ አስኪያጃቸው ጋር እንዲቀርቡ ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ አዘዘ
- በጠ/ቤ/ክህነቱ ኦዲት የተረጋገጠውን
የ1.8 ሚሊዮን ብር ጉድለት ሲያጣጥሉ የቆዩት ሥ/አስኪያጁ ጉድለቱን አምነዋል፤ - ሥራ አስኪያጁ ሙሰኝነትን በተቃወሙ
ሰባት የደብር አለቆች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፈዋል፤ - ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ
የነበረው ደብሩ በቋቱ የቀረው ከብር 70,000 አይበልጥም፤
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 25/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 6/2012/ READ IN PDF):- የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከሚካሄድ
ድረስ በስምንት ተጨማሪ ብፁዓን አባቶች እንዲጠናከር የተደረገውና ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩን ጨምሮ ዐሥራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ
ጳጳሳትን በአባልነት የያዘው ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት፣ መስከረም 25 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው÷
የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና
ምእመናን ተወካዮች በሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ጉዳይ በደብሩ
አስተዳዳሪ፣ በሕንጻ አሠሪው ኮሚቴ ሊቀ መንበር፣ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ በየደረጃው
ስለቀረቡት አቤቱታዎች እንዲያስረዱ ከጠራቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጋር መወያየቱ ተሰምቷል፡፡

በዚሁ ውይይት የሕንጻ ሥራው ሒሳብና የግንባታ ጥራቱ የደብሩ የሰበካ ጉባኤ አባላት በምእመኑ ተሳትፎ
ባስመረጧቸው ባለሞያዎች እንዲመረመርና በተገኘው ጉድለት ላይ ሓላፊነት የሚወስዱት ተለይተው ርምጃ እንዲወሰድባቸው፤ በ1998 ዓ.ም
ተጀምሮ በሁለት ዓመት እንዲጠናቀቅ የታቀደው ሕንጻ ስምንት ዓመት የመጓተቱን ምክንያትና በአስቸኳይ ስለሚፈጸምበት ኹኔታ፤ የደብሩ አስተዳዳሪና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በምእመናኑ የተመረጠውን ሰበካ ጉባኤ በተደጋጋሚ
ስለማገዳቸውና ያልተገቡ አሠራሮች እንዲታረሙ ጥያቄ በሚያቀርቡ የደብሩ አገልጋዮችና ምእመናን እንዲጉላሉ ስለማድረጋቸው በተወካዮቹ
ለቀረቡት ጥያቄዎች ብፁዕነታቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡

ይኹንና ብፁዕነታቸው ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ በሰጡት ምላሽ “እኔ ብቻዬን ለማስረዳት አልችልም” በሚል የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳን ይዘው ለመቅረብ
ፈቃድ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱም ብፁዕነታቸው ሥራ አስኪያጁን ይዘው በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ በሚካሄደው መደበኛ ስብሰባ
ላይ እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ “የብፁዕነታቸው ምላሽ የሚጠበቅ
ነው” የሚሉት የጉዳዩ ተከታታዮች ብቻቸውን የተጠሩት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የሀገረ ስብከቱን
ጸሐፊና የቁጥጥር አገልግሎት ሓላፊ አበል ከፍለው ይዘው ለመሄድ እያግባቧቸው መኾኑን ተናግረዋል፡፡ በሊቃውንት የተጠናከረውን የሀ/ስብከቱን
አስተዳደር ጉባኤ ሲያዳክሙ የቆዩት ሥራ አስኪያጁ አብረዋቸው እንዲቀርቡ የሚያግባቧቸው ሁለቱ ሓላፊዎች ሥራ አስኪያጁ በብቸኝነት
ከወሰዷቸው ርምጃዎች የተለየ አቋም እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡

ለአብነት ያህል ሥራ አስኪያጁ ከሳባ ደ/ኀ/ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ጋር በማበር ከአንድም
ሁለት ጊዜ በምእመናን የተመረጡትን ሰበካ ጉባኤ አባላት ያገዱበትን ደብዳቤ ሲጽፉ የጸሐፊው አቋም (ፓራፍ አለማድረግን ጨምሮ) የተለየ
ነበር፡፡ ሥራ አስኪያጁ የግዳጅ ጡረታ እንዲወጡ በተደረጉት የቀድሞው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቁጥጥር አገልግሎት ሓላፊ በኵረ ትጉሃን
ዓለም አታላይ በተመራው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሒሳብ የማጣራት ሥራ የብር 1.8 ሚሊዮን ጉድለት ያረጋገጠውን የኦዲት ግኝት “ትክክል አይደሉም፤ ገንዘብ አልጎደለም፤ ጎደለ የሚል ወሬኛ ነው፤ ለቤተ
ክርስቲያን የማያስብ ነው” እያሉ በዐውደ ምሕረት ሳይቀር ሲያጥላሉ የሀ/ስብከቱ ቁጥጥር ግን ጉድለቱን አምነው የፈረሙ መሆናቸው
ተገልጧል፡፡

![]() |
| አባ አረጋዊ ነሞምሳ |
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቁጥጥር አገልግሎት ሓላፊ የኦዲት ሪፖርቱን ማቅረባቸውን ተከትሎ ይቅርታ እንዲጠይቁ
በቀድሞው ፓትርያርክ መጋቤ ሥርዐት በእነ ሙሉጌታ በቀለ እና በተቆጣጣሪው መሐንዲስ ሰሎሞን ካሳዬ መገደዳቸውን የሚያውቁት ሥራ አስኪያጁ÷
የፕሮጀክት አማካሪ መሐንዲሶች ፈቃድና ይኹንታ ሳይገኝና ተቋራጩ ምንም ዐይነት የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሳያቀርብ በሚሰጠው ብድርና
በሚፈጸመው ክፍያና ይህም እንዲከናወን ለሚተባበሩት የሕንጻ አሠሪው ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሕገ ወጥ ድርጊት ሽፋን በመስጠታቸው ከምሥረታው
ጀምሮ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የተሰበሰበ ብር 11,388,096.23 ተቀማጭ የነበረው ደብሩ ዛሬ በቋቱ ውስጥ የሚገኘው ገንዘብ ከብር
70,000 እንደማይበልጥ ነው ምንጮቻችን የሚናገሩት፡፡

በሌላ በኩል የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ በትናንትናው ዕለት እንዳደረጉት በሙስና
የተበላሸ አስተዳደራቸውን በሚቃወሙ ሰባት የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አለቆች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለመጻፍ
አላገዳቸውም፡፡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው መነሻ ሁሉም የድሬዳዋ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የሽኒሌ መካነ መቃብር ይዞታን በጋራ አስከብረውና
አጥር አሳጥረው፣ ከሁሉም አድባራት ተውጣጥቶ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት ቤተ ጸሎት ሠርተው እያጠኑ የሚጠቀሙበትና በአንድነት የሚያስተዳድሩበት
የጋራ ኮሚቴ ከሚያውቀው የባንክ አካውንት ውጭ ሌላ አካውንት መከፈቱንና የሠራተኛ ቅጥር መፈጸሙን በመቃወም ለሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት
የጻፉት ደብዳቤ ነው፡፡ የአድባራቱ አስተዳዳሪዎች ጥያቄ ባለቤትም ባለ ይዞታም የኾኑበትን መካነ መቃብር በአንድነት ማስተዳደራቸውን
እንዲቀጥሉ ነው፡፡

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ኅልፈት በኋላ ቀድሞም ቢኾን ከውጭ ጉዞዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ሙስናዎችና
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሱ ተግባራት እንደሚፈጸሙበት የሚነገረውን የልዩ ጽ/ቤቱን የውጭ ግንኙነት በበላይ ሓላፊነት ከመምራት ባሻገር
የዓለም አብያተ ክርስቲያን ፕሬዝዳንት እና የዓለም አብያተ ክርስቲያን የክብር ፕሬዝዳንት ቢሮ ዋና ጸሐፊ የኾኑት ብፁዕነታቸው የሀገረ
ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በኾኑበት ባለፉት ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ የተገኙት በዓመት ሁለት ጊዜ በቁሉቢ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ
በዓል ነው፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ለሀ/ስብከቱ ሠራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እንኳን የሒሳብና በጀት ክፍሉ በየወሩ ወደ አዲስ
አበባ ለፊርማ መምጣት ስላለበት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለመጓጓዣ እና አበል ከብር 24,000 ያላነሰ ወጪ ተደርጓል፡፡

ይህም ኾኖ የከተማው ነዋሪዎች፣ የአጥቢያው ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ካህናት በሀገረ
ስብከቱና በሳባ ደ/ኀ/ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዳለው ዐይነት አስከፊ የሙስና ወንጀሎችንና የአስተዳደር በደሎችን የተመለከቱ
አቤቱታዎችን በሚያቀርብቡት ወቅት የቅርብ መረጃ የሌላቸው ብፁዕነታቸው የሚሰሙት ምእመኑን “ወሬኞችና አድመኞች፤ የዲያብሎስ ቡችሎች” እያሉ በዐውደ ምሕረት የሚሳደቡትን፣ ሲያሻቸውም በጥቅም ከተቆራኟቸው
አንዳንድ የፍትሕ አካላት እና የጸጥታ ኀይሎች ጋር በመመሳጠር ምእመኑን የሚያጉላሉትን፣ በሌሎች የቢዝነስ ሥራዎቻቸው በገንዘብ እያጨበረበሩ
መከሰስን የለመዱትን (ብርሃኔ መሐሪ ሰሞኑን በአንድ የጭነት ማመላሻ
ማኅበር የብር 90,000 የማጭበርበር ክስ እንደተመሠረተባቸው)፣ እነአእመረ አሸብር እንዳሻቸው ደብዳቤ እየለቀለቁ የሚልኳቸውን
እንደ አሰግድ ሣህሉ ያሉ የለየላቸው መናፍቃን የሚያስተናግዱ “ሌቦችና
ነውረኞች” ነው፡፡

በዚህም ያዘነውና የተቆጣው አገልጋይና ምእመን ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር መጨረሻ በአድራሻ ለብፁዕነታቸው
በጻፈው ደብዳቤ በደሉ ሊታገሠው ከሚችለው በላይ እያለፈ በመኾኑ አስፈላጊው ማስተካከያ ካልተደረገ ለሚፈጠረው ችግር ሓላፊነቱን እንደማይወስድ
ብፁዕነታቸውን አሳስቧል፡፡ ከዚያም ወዲህ የባሰበት እንጂ የተሻለ ነገር ባለማየቱ በሰሞኑ ጥያቄው ሙሰኛ ሓላፊዎች እንዲወገዱ፣ ሀገረ
ስብከቱን በቅርበት እየከታተለ አባታዊ ቡራኬ የሚሰጠው ብፁዕ አባት እንዲሰጠው ለቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡