የኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚና ሰባት ኃላፊዎች ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ

–    ቃላቸውን ሰጥተው በ10 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀዋል
–    በተርሚናል ውስጥ ያሉ ሱቆች ጨረታ ጊዜ ማለፉ እያነጋገረ ነው

በታምሩ ጽጌ

ከዓመታት በፊት ወጥቶ ከነበረ ጨረታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ዓለሙና ሌሎች ሰባት የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡