የኢንተርኔት አጠቃቀማችን “ነጻነት” ጉዳይ

ኤፍሬም እሸቴ

የኢንተርኔት መብት አያያዝ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሁናቴ በተመለከተ በየዓመቱ ጥናት የሚያደርገው “ፍሪደም ሐውስ” የሚባለው ታዋቂው የአሜሪካ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የ2012 ዘገባውን ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት እንዳላቸው እና ዓመታዊ ሪፖርታቸው በጉጉት እንደሚጠበቀው “ሒዩማን ራይትስ ዎች”ን እንደመሳሰሉት ድርጅቶች ሁሉ “Freedom House”ም ሚዛን የሚደፋ ሪፖርት በማቅረብ የሚታወቅ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት የተቋቋመ የአሜሪካ ድርጅት ነው።