የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ የዲሞክራሲ ጮራ ስትወጣ
ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፦ ነጻነት ለሃገሬ)
በድጋሚ እውነት፤ ኃይልን ለተነፈጉ
ላለፉት በርካታ ዓመታት ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች ዕውነትን ስናገር ነበር። የጦማሬ ገጼ መግቢያ መስመሩ ”ለሰብአዊ መብት ተሟገት። ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች እውነትን መስክር” ነው የሚለው። ይህ ደሞ ልዩ ትርጉም ያለው፤ ጠንካራ ሞራልና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ አላግባብ የሚጠቀሙበትን፤ ከመጠን በላይ ለሚተማመኑበት ኢሰብአዊ ድርጊት ማስገንዘቢያ የሆነ ስንኝ ነው። ለባለስልጣናት ነን ባዮች እውነትን መናገር፤ ተናጋሪው በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ስልጣናቸው የተዘረጋው በሃሰት ላይ መሆኑን ምስክርነቱን ያረጋግጣል።