መንገዶች ባለሥልጣን የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን ገመገመ
• የ21 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶችን ለመስጠት ጨረታ ያወጣል
በውድነህ ዘነበ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሲያካሂድ የቆየውን የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ትናንት አጠናቀቀ፡፡ ባለሥልጣኑ ያወጣው የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መርሐ ግብር እንደሚያመለክተው፣ በቀጣይነት የውጭ ኮንትራክተሮችን የሥራ አፈጻጸም መገምገም ይጀምራል፡፡