መንግሥት ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚከለክል ሕግ ለማውጣት እያሰበ ነው

በዮናስ አብይ

በአገሪቱ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉና ሃይማኖታዊ ግጭቶችን እየፈጠሩ ነው የሚባሉ ማናቸውም ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ምስሎች፣ ጥቅሶች፣ ድምፅን የሚበክሉ የጐዳና ላይ ስብከቶችና መዝሙሮች፣ ከሕዝባዊ ቦታዎች የሚከለክል አዲስ ሕግ አውጥቶ በሥራ ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡