ሼክ አል አሙዲ ለመንግሥት ባለሥልጣናት

•    ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን

•    መንግሥት ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው

•    መንግሥትን የንግዱን ነገር ለእኛ ይተውልን

በዮሐንስ አንበርብር

ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ መዋለ ነዋያቸውን ካፈሰሱባቸው ፕሮጀክቶች ትልቁ ያሉትን የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካ ገንብቶ ለማስረከብ ከመረጡት የጣሊያን ኩባንያ ጋር ለመፈራረም ባሰናዱት ዝግጅት ላይ፣ በቅርቡ የተሾሙትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ መንግሥት ለንግዱ ኅብረተሰብ ማድረግ የሚጠበቅበትንና የንግዱ ኅብረተሰብ ከመንግሥት የሚጠብቀው ነው ያሉትንም አዋዝተው ተናግረዋል፡፡